Ethiopian Engineering Corporation

News

የኮርፖሬሽኑ ስኬት የሚለካው በገነባቸው ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይሆን በገነባው የሥነ-ምግባርና የታማኝነት ባህል ጭምር መሆኑ ተመለከተ::

(ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም) ፣ አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC)፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ ለ22 ተኛ  ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን፡- “ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር ” በሚል መሪ- ቃል በዋናው ቢሮ አክብሯል፡፡ መድረኩ፣ የፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተልዕኮና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት በተለይም ሙስናን አስቀድሞ መከላከል፣ የሥነ-ምግባር ብቃትን ማጎልበት፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት አሰራርን ማረጋገጥን መሰረት በማድረግ፤ የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቀንን  እንዲያከብሩና ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያስቻለ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ኮርፖሬሽኑ (EEC) ለአጠቃላይ ሠራተኞች የኮሚሽኑን መሪ-ቃል በማስተዋወቅ፤ የሥነ-ምግባር ብቃት ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት፣ የውስጥ አሰራር ስርዓት ግምገማ ማድረግ፣ የቃል-ኪዳን መድረክና የሥነ-ምግባር አርዓያነትን በመሸለምና በማስተዋወቅ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ በመድረኩ ኮርፖሬሽኑ (EEC) በአሁኑ ወቅት በማማከሩና በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ በአጠቃላይ ከ436 በላይ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ እንደሚገኙና በቅንጅታዊ አሰራርና በውጤታማ አፈጻጸም የምንታወቅ የመንግሥት የልማት ድርጅት መሆን እንዳለብን አሰራራችንም ንጽህናን የተከተለ መሆን ይኖርበታል ተብሏል፡፡ በዚህም ተቋማዊ አሰራሮችን አድምቶ በመስራት፤ ለሙስና አጋላጭ መንገዶችን ለመዝጋት ይቻለናል፤ ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡ በመጨረሻም ባለ አምስት ነጥብ የኮርፖሬሽኑን ሠራተኞች የአቋም መግለጫ በማውጣት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ስኬት የሚለካው በገነባቸው ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይሆን በገነባው የሥነ-ምግባርና የታማኝነት ባህል ጭምር መሆኑ ተመለከተ:: Read More »

This is what defines us: ahead of schedule, under budget, and safely.

We are proud to announce the successful completion of the Design-Build of a B+G+2 Office Building, including site works, master plans for three port developments (Gurer, Bahirdar, and Gorgora), and a detailed design study for Ethiopian Shipping and Logistics(ESL). ✅ Delivered ahead of schedule, ✅ Completed under budget, and ✅ Achieved more than half a million safe man-hours without incident. Thank you to every team member who contributed to this success. Your dedication continues to raise the bar for what’s possible at EEC. COLLABORATE | INNOVATE | DELIVER

This is what defines us: ahead of schedule, under budget, and safely. Read More »

ኮርፖሬሽኑ (EEC) በብሔራዊ ባንክ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግንባታዎች ላይ በማማከር መስክ እየሰራ ይገኛል

ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም፣ (ድሬዳዋ) ፤ ብሔራዊ ባንክ እያስገነባቸው ካሉ ቅርንጫፎች መካከል፣ በድሬዳዋ ሳይት ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው፤ ተጠሪ መሃንዲስ ዮናስ መኮንን (ኢንጅነር) እንደገለጹት፤ ግንባታው እየተከናወነ ያለው በ12 ሔክታር ስፋት ላይ መሆኑንና ከዚህ ውስጥ 3.4 ሔክታር በሚያክለው ቦታ ላይ B+G+6 ወለል በመገንባት ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ሒደት ኢኮኖሚው ውስጥ የማይፈለጉ የገንዘብ ኖቶች በሚኖሩበት ወቅት፣ ይኸውም “ፎርጅድ ገንዘቦች” እና በከፍተኛ እርጅና ውስጥ ያሉ የገንዘብ ኖቶች በሚኖሩበት ወቅት፣ ወደኢኮኖሚው እንዳይገቡ ያንን ማስወገድ የሚችል ሲስተም የሚገጠምለት ህንጻ ጭምር እንደሆነ ተጠሪ መሃንዲሱ አብራርተዋል፡፡ ህንጻው ለየት የሚያደርገው በአውሮፓ ላይ አለ የሚባልና በመስኩ አሁን የተደረሰበትን ደረጃ 13 የ“Volt” ደረጃን የሚያሟላ ህንጻ መሆኑንም ዮናስ መኮንን (ኢንጅነር) ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የግንባታውን ጥራት አስመልክቶም፤ ከፍተኛ ደህንነትና ጥበቃ የሚደረግባቸው ዞኖችና የባንኪንግ ሲስተሙ አበይት የካሽ እንቅስቃሴዎች የሚከናወኑበት እንደመሆኑ፤ ሥራውም በከፍተኛ ጥራት መሰራቱንና የግድግዳ ስፋቱ ብቻ አንድ ሜትር ውፍረት ባለው አርማታ የተሞላ መሆኑን፤ ጣሪያውም በተመሳሳይ መልኩ በአንድ ሜትር ውፍረት መሞላቱን፤ ከዚህ በተጨማሪም የካሽ ሴንተሩን ሥራ የሚያካሂደው የጀርመን ኩባኒያ ደግሞ ከውጪ የሚያስገባቸው፤ ባንኩ ከፍንዳታና ከፍተኛ የመሰርሰር አቅም ካላቸው ማሽኖች ’ራሱን መከላከል እንዲችል ዲዛይን ተደርጎ፤ በዚያ መልኩ እየተሞላ መሆኑን ገልፀዋል። የ“ቮልት” (Volt) ክፍሉ “T50” በሚባል ከፍተኛ የኮንክሪት የጥራት ደረጃ እየተሰራ ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ (EEC) በብሔራዊ ባንክ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግንባታዎች ላይ በማማከር መስክ እየሰራ ይገኛል Read More »

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የመገጭ ግድብና መስኖ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ጎበኙ

የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል። ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17,000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ (Diversion) ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ”። ጠ/ሚ  ዶ/ር አብይ አህመድ ኮርፖሬሽኑ (EEC) በዲዛይንና ሱፐርቪዥን እየተሳተፈ እንደሆነ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የመገጭ ግድብና መስኖ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ጎበኙ Read More »

የአውሮፕላን ማረፊያው መገንባት በትራንስፖርት ዕጦት ይገጥማቸው የነበረውን እንግልት እንደሚቀርፍላቸው የነጌሌ ቦረና ነዋሪዎች ተናገሩ

ኮርፖሬሽኑ (EEC) በዲዛይንና ማማከር ሥራ እየተሳተፈበት ያለው የነጌሌ ቦረና የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት ከወራት ባልበለጠ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ይጀምራል:: የነጌሌ ቦረና አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ተቆጣጣሪ መሃንዲስ ናርዶስ አማረ (ኢንጅነር) በበኩላቸው፤ በ1.5 ቢልየን የኢትዮጵያ ብር በመገንባት ላይ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት፣ በአገራችን ካሉ ሌሎች የአየር መንገዶች በተለየ ሁናቴ፣ እያንዳንዳቸው አራት አራት አውሮፕላኖችን ማሳረፍ የሚችሉ ባለ ሁለት ይኸውም ሚሊተሪና ሲቪል አውሮፕላን ማቆሚያ (Apron) ሆኖ፤ በአጠቃላይ ወደአራት ኪሎሜትር የሚደርስ ርዝመት ያለው የአውሮፕላን መንደርደሪያ (Runway) እየተገነባ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

የአውሮፕላን ማረፊያው መገንባት በትራንስፖርት ዕጦት ይገጥማቸው የነበረውን እንግልት እንደሚቀርፍላቸው የነጌሌ ቦረና ነዋሪዎች ተናገሩ Read More »

EEC Annual Corporate Event 2025

EEC Annual Corporate Event 2025

Celebrating outstanding achievements and setting one vision and legacy under one roof with one team — that was the spirit of our Annual Corporate Event 2025. It was a moment of reflection, recognition, and unity as we came together to celebrate the people and the progress that continue to shape our journey at EEC. With every step forward, we reaffirm our commitment: Together, we build Ethiopia. And as our country marks the historic inauguration of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD), we proudly share in the spirit of determination and dedication that drives great achievements for Ethiopia. COLLABORATE | INNOVATE | DELIVER

EEC Annual Corporate Event 2025 Read More »

የሀዋሳ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እየተሰራ ነው

ክትትል እየተሰራ ነው ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ሀዋሳ) ፤ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) በሀዋሳ ከተማ በግንባታ ላይ ያለው የመንገድ ሥራ ግንባታ ፕሮጀክት ጥራቱን ጠብቆ በማጠናቀቅ የከተማውን የትራፊክ ፍሰት እንዲያሳልጥ  ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ላይ እንደመገኘቱ፣ ወደከተማዋ የሚመጡ ጎብኚዎችን ጨምሮ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ፣ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን ጭምር ያካተተ ነው። ይህ ፕሮጀክት 5.43 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን ለአብነትም በሎት 1 ላይ  በጠቅላላው 26 ሜትር ስፋት ያለውና በአንድ ጊዜ በሁለቱም አቅጣጫ በድምሩ ስምንት (8) ተሽከርካሪዎችን ማሳለፍ እንዲችል ሆኖ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ከሳውዝ ስፕሪንግ እስከ ሐይሌ ሪዞርት መጋጠሚያ ድረስ ያለው መንገድ የእግረኛ መንገዱን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ የአፈር ቆረጣው ሥራ ተጠናቆ፤ የመጨረሻ ንጣፍ (Base Course) ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ኮርፖሬሽናችን (EEC) በሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ላይ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ተሳትፎ እያደረገ ሲሆን ከከተማው ወደ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደውን መንገዱን ጨምሮ ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችም ላይ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ጉልህ አሻራውን ማሳረፉ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ፣ ጅማ፣ አዳማና ቢሾፍቱ ከተሞች የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ኮርፖሬሽናችን (EEC) እንደሚሳተፍ መዘገባችን ይታወቃል።

የሀዋሳ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እየተሰራ ነው Read More »

We Got Our First Private Client for the Construction Sector!!

May 21,2025 (Addis Ababa) We are delighted to announce that we have signed a contract with Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church  Client:  Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church  Consultant: Zeleke Belay Architect PLC  Scope: Construction works of the structure works of Eastern Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church 2B+G+15 multipurpose building  Amount:  803,970,655.48 ETB   Duration: 540 calendar days  Location: Addis Ababa, Ethiopia  We thank our team for their dedicated work on securing this project.  We wish good luck and success to the entire team to be involved.

We Got Our First Private Client for the Construction Sector!! Read More »

EEC የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከልን መልሶ ለማደራጀት የዲዛይንና የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራረመ

(መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤ ኮርፖሬሽኑ በትናንትናው ዕለት ማለትም መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም የውል ስምምነቱን የተፈራረመው፤ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ሲሆን የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የጂኦሳይንስ መረጃን ለማመንጨት እና የማዕድናት ናሙና መመርመሪያ በመሆን የሚያገለግለውን፤ የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከልን መልሶ ለማደራጀት የሚያስችል ተግባርን ለማከናወን ነው፡፡ የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከል፣ የጂኦሳይንስ መረጃን በማመንጨትና ማዕድናትን በመመርመር፤ ለረጅም ጊዜ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን የማዕከሉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና መልሶ ለማደራጀት፤ ከሰባት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ፤ ከኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) ጋር የፕሮጀክት ስምምነቱ ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት፣ የኮርፖሬሽናችን (EEC) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽመልስ እሸቱ (ኢንጂነር) እና የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ ተፈራመዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረትም ግንባታውን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል፡፡

EEC የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከልን መልሶ ለማደራጀት የዲዛይንና የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራረመ Read More »

“የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

(መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤ የኮሪደር ልማት ሥራ ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማት ሥራ ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ብቻ በኮሪደር ልማት አማካይነት ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ መሰራቱን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶችም ተካተው መከናወናቸውን አንስተዋል ።አክለውም በሁሉም የክልል ከተሞች አስደማሚ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በማስታወስ፤ ለአብነትም በሐረር ከተማ በዜጎች ተሳትፎ የተከናወነው ሥራ ለሁሉም ከተሞች ምሳሌ መሆን የሚችል ተግባር እንደሆነ መግለጻቸውን ጨምሮ ኢዜአ ዘግቧል። ተቋማችን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) የመዲናችን አዲስ አበባን የኮሪደር ልማት ሥራ ጨምሮ በጂማ፣ በሐዋሳ፣ በአዳማና በቢሾፍቱ ከተሞች ባሉ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በአማካሪነት በመስራት ላይ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

“የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Read More »

Scroll to Top