Ethiopian Engineering Corporation

የሀዋሳ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እየተሰራ ነው

ክትትል እየተሰራ ነው

ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ሀዋሳ) ፤

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) በሀዋሳ ከተማ በግንባታ ላይ ያለው የመንገድ ሥራ ግንባታ ፕሮጀክት ጥራቱን ጠብቆ በማጠናቀቅ የከተማውን የትራፊክ ፍሰት እንዲያሳልጥ  ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ፕሮጀክቱ የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ላይ እንደመገኘቱ፣ ወደከተማዋ የሚመጡ ጎብኚዎችን ጨምሮ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ፣ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን ጭምር ያካተተ ነው።

ይህ ፕሮጀክት 5.43 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን ለአብነትም በሎት 1 ላይ  በጠቅላላው 26 ሜትር ስፋት ያለውና በአንድ ጊዜ በሁለቱም አቅጣጫ በድምሩ ስምንት (8) ተሽከርካሪዎችን ማሳለፍ እንዲችል ሆኖ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ከሳውዝ ስፕሪንግ እስከ ሐይሌ ሪዞርት መጋጠሚያ ድረስ ያለው መንገድ የእግረኛ መንገዱን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ የአፈር ቆረጣው ሥራ ተጠናቆ፤ የመጨረሻ ንጣፍ (Base Course) ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽናችን (EEC) በሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ላይ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ተሳትፎ እያደረገ ሲሆን ከከተማው ወደ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደውን መንገዱን ጨምሮ ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችም ላይ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ጉልህ አሻራውን ማሳረፉ ይታወሳል፡፡

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ፣ ጅማ፣ አዳማና ቢሾፍቱ ከተሞች የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ኮርፖሬሽናችን (EEC) እንደሚሳተፍ መዘገባችን ይታወቃል።

Scroll to Top