Ethiopian Engineering Corporation

EEC የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከልን መልሶ ለማደራጀት የዲዛይንና የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራረመ

(መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤

ኮርፖሬሽኑ በትናንትናው ዕለት ማለትም መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም የውል ስምምነቱን የተፈራረመው፤ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ሲሆን የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የጂኦሳይንስ መረጃን ለማመንጨት እና የማዕድናት ናሙና መመርመሪያ በመሆን የሚያገለግለውን፤ የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከልን መልሶ ለማደራጀት የሚያስችል ተግባርን ለማከናወን ነው፡፡

የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከል፣ የጂኦሳይንስ መረጃን በማመንጨትና ማዕድናትን በመመርመር፤ ለረጅም ጊዜ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን የማዕከሉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና መልሶ ለማደራጀት፤ ከሰባት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ፤ ከኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) ጋር የፕሮጀክት ስምምነቱ ተፈርሟል፡፡

ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት፣ የኮርፖሬሽናችን (EEC) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽመልስ እሸቱ (ኢንጂነር) እና የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ ተፈራመዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረትም ግንባታውን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Scroll to Top