ኮርፖሬሽኑ (EEC) በዲዛይንና ማማከር ሥራ እየተሳተፈበት ያለው የነጌሌ ቦረና የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት ከወራት ባልበለጠ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ይጀምራል::
የነጌሌ ቦረና አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ተቆጣጣሪ መሃንዲስ ናርዶስ አማረ (ኢንጅነር) በበኩላቸው፤ በ1.5 ቢልየን የኢትዮጵያ ብር በመገንባት ላይ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት፣ በአገራችን ካሉ ሌሎች የአየር መንገዶች በተለየ ሁናቴ፣ እያንዳንዳቸው አራት አራት አውሮፕላኖችን ማሳረፍ የሚችሉ ባለ ሁለት ይኸውም ሚሊተሪና ሲቪል አውሮፕላን ማቆሚያ (Apron) ሆኖ፤ በአጠቃላይ ወደአራት ኪሎሜትር የሚደርስ ርዝመት ያለው የአውሮፕላን መንደርደሪያ (Runway) እየተገነባ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡


