Ethiopian Engineering Corporation

ኮርፖሬሽኑ (EEC) በብሔራዊ ባንክ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግንባታዎች ላይ በማማከር መስክ እየሰራ ይገኛል

ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም፣ (ድሬዳዋ) ፤

ብሔራዊ ባንክ እያስገነባቸው ካሉ ቅርንጫፎች መካከል፣ በድሬዳዋ ሳይት ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው፤ ተጠሪ መሃንዲስ ዮናስ መኮንን (ኢንጅነር) እንደገለጹት፤ ግንባታው እየተከናወነ ያለው በ12 ሔክታር ስፋት ላይ መሆኑንና ከዚህ ውስጥ 3.4 ሔክታር በሚያክለው ቦታ ላይ B+G+6 ወለል በመገንባት ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህ ሒደት ኢኮኖሚው ውስጥ የማይፈለጉ የገንዘብ ኖቶች በሚኖሩበት ወቅት፣ ይኸውም “ፎርጅድ ገንዘቦች” እና በከፍተኛ እርጅና ውስጥ ያሉ የገንዘብ ኖቶች በሚኖሩበት ወቅት፣ ወደኢኮኖሚው እንዳይገቡ ያንን ማስወገድ የሚችል ሲስተም የሚገጠምለት ህንጻ ጭምር እንደሆነ ተጠሪ መሃንዲሱ አብራርተዋል፡፡

ህንጻው ለየት የሚያደርገው በአውሮፓ ላይ አለ የሚባልና በመስኩ አሁን የተደረሰበትን ደረጃ 13 የ“Volt” ደረጃን የሚያሟላ ህንጻ መሆኑንም ዮናስ መኮንን (ኢንጅነር) ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የግንባታውን ጥራት አስመልክቶም፤ ከፍተኛ ደህንነትና ጥበቃ የሚደረግባቸው ዞኖችና የባንኪንግ ሲስተሙ አበይት የካሽ እንቅስቃሴዎች የሚከናወኑበት እንደመሆኑ፤ ሥራውም በከፍተኛ ጥራት መሰራቱንና የግድግዳ ስፋቱ ብቻ አንድ ሜትር ውፍረት ባለው አርማታ የተሞላ መሆኑን፤ ጣሪያውም በተመሳሳይ መልኩ በአንድ ሜትር ውፍረት መሞላቱን፤ ከዚህ በተጨማሪም የካሽ ሴንተሩን ሥራ የሚያካሂደው የጀርመን ኩባኒያ ደግሞ ከውጪ የሚያስገባቸው፤ ባንኩ ከፍንዳታና ከፍተኛ የመሰርሰር አቅም ካላቸው ማሽኖች ’ራሱን መከላከል እንዲችል ዲዛይን ተደርጎ፤ በዚያ መልኩ እየተሞላ መሆኑን ገልፀዋል።

የ“ቮልት” (Volt) ክፍሉ “T50” በሚባል ከፍተኛ የኮንክሪት የጥራት ደረጃ እየተሰራ ነው፡፡

Scroll to Top