Ethiopian Engineering Corporation

የኮርፖሬሽኑ ስኬት የሚለካው በገነባቸው ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይሆን በገነባው የሥነ-ምግባርና የታማኝነት ባህል ጭምር መሆኑ ተመለከተ::

(ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም) ፣ አዲስ አበባ፤

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC)፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ ለ22 ተኛ  ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን፡- “ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር ” በሚል መሪ- ቃል በዋናው ቢሮ አክብሯል፡፡

መድረኩ፣ የፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተልዕኮና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት በተለይም ሙስናን አስቀድሞ መከላከል፣ የሥነ-ምግባር ብቃትን ማጎልበት፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት አሰራርን ማረጋገጥን መሰረት በማድረግ፤ የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቀንን  እንዲያከብሩና ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያስቻለ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ (EEC) ለአጠቃላይ ሠራተኞች የኮሚሽኑን መሪ-ቃል በማስተዋወቅ፤ የሥነ-ምግባር ብቃት ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት፣ የውስጥ አሰራር ስርዓት ግምገማ ማድረግ፣ የቃል-ኪዳን መድረክና የሥነ-ምግባር አርዓያነትን በመሸለምና በማስተዋወቅ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ኮርፖሬሽኑ (EEC) በአሁኑ ወቅት በማማከሩና በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ በአጠቃላይ ከ436 በላይ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ እንደሚገኙና በቅንጅታዊ አሰራርና በውጤታማ አፈጻጸም የምንታወቅ የመንግሥት የልማት ድርጅት መሆን እንዳለብን አሰራራችንም ንጽህናን የተከተለ መሆን ይኖርበታል ተብሏል፡፡

በዚህም ተቋማዊ አሰራሮችን አድምቶ በመስራት፤ ለሙስና አጋላጭ መንገዶችን ለመዝጋት ይቻለናል፤ ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡

በመጨረሻም ባለ አምስት ነጥብ የኮርፖሬሽኑን ሠራተኞች የአቋም መግለጫ በማውጣት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡

Scroll to Top