የካቲት 29, 2017 (አዲስ አበባ)፤
የኢትዮ – ጅቡቲ ባቡር መንገድ ካሉት 20 የባቡር ጣቢያዎች አንዱ የሆነው ይህ ጣቢያ ማስፋፊያውን የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) የጥናት፣ ዲዛይንና ማማከር ስራ እየሰራ ይገኛል።
የግብዓት ማሰባሰቢያ አውደ ጥናት ተዘጋጅቶ ሰፊ የባለሞያዎች ውይይት ማድረግ የተቻለ ሲሆን በመድረኩም ብዙ ገንቢ ሀሳቦች ተነስተዋል።
የእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያ የሚገኝበት አካባቢ ለአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ የገቢና ወጪ ንግዶችን ከማቀላጠፉ በተጨማሪ ከቢሾፍቱ ከተማ በቅርብ ርቀት እየተገነባው ያለው አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያን፣ የሞጆና የቃሊቲ ደረቅ ወደቦችን በማቀናጀት የሀገር ውስጥና የውጪ የንግድ ልውውጥን በየብስ፣ በአየርና በባህር ትራንስፖርት በማሳለጥና በማዘመን የእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያን ወደ ነጻ የንግድ ቀጠናነት (Free Trade Zone) ለማሳደግ ያለመ ፕሮጀክት ነው።
ኮርፖሬሽኑ (EEC) በሀገር ውስጥና በአፍሪካ በተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ በጎ አሻራውን እያኖረ ሲሆን ይህንንም ታላቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለውን ፕሮጀክት የዲዛይን ስራውን አለም አቀፍ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
በቅርቡ የቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ግንባታ ፕሮጀክትን በግማሽ ቢልዮን ብር በጥራት ገንብቶ ለማስረከብ ኮርፖሬሽናችን (EEC) ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ጋር መፈራረሙን መዘገባችን ይታወሳል።