Ethiopian Engineering Corporation

News

ለእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያ ማስፋፊያና መሪ እቅድ ንድፍ (Master Plan Design) የግብዓት ማሰባሰብ ስራ ተጀመረ

የካቲት 29, 2017 (አዲስ አበባ)፤ የኢትዮ – ጅቡቲ ባቡር መንገድ ካሉት 20 የባቡር ጣቢያዎች አንዱ የሆነው ይህ ጣቢያ ማስፋፊያውን የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) የጥናት፣ ዲዛይንና ማማከር ሾል እየሰራ ይገኛል። የግብዓት ማሰባሰቢያ አውደ ጥናት ተዘጋጅቶ ሰፊ የባለሞያዎች ውይይት ማድረግ የተቻለ ሲሆን በመድረኩም ብዙ ገንቢ ሀሳቦች ተነስተዋል። የእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያ የሚገኝበት አካባቢ ለአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ የገቢና ወጪ ንግዶችን ከማቀላጠፉ በተጨማሪ ከቢሾፍቱ ከተማ በቅርብ ርቀት እየተገነባው ያለው አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያን፣ የሞጆና የቃሊቲ ደረቅ ወደቦችን በማቀናጀት የሀገር ውስጥና የውጪ የንግድ ልውውጥን በየብስ፣ በአየርና በባህር ትራንስፖርት በማሳለጥና በማዘመን የእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያን ወደ ነጻ የንግድ ቀጠናነት (Free Trade Zone) ለማሳደግ ያለመ ፕሮጀክት ነው። ኮርፖሬሽኑ (EEC) በሀገር ውስጥና በአፍሪካ በተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ በጎ አሻራውን እያኖረ ሲሆን ይህንንም ታላቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለውን ፕሮጀክት የዲዛይን ስራውን አለም አቀፍ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርግ አስታውቋል። በቅርቡ የቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ግንባታ ፕሮጀክትን በግማሽ ቢልዮን ብር በጥራት ገንብቶ ለማስረከብ ኮርፖሬሽናችን (EEC) ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ጋር መፈራረሙን መዘገባችን ይታወሳል። 

ለእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያ ማስፋፊያና መሪ እቅድ ንድፍ (Master Plan Design) የግብዓት ማሰባሰብ ስራ ተጀመረ Read More »

የዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ  እየተከበረ ይገኛል

(የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤ 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ እየተከበረ ያለው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሲሆን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ ይህን ዘመን አይሽሬና የመላው ጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፣ የድሉን ታሪካዊ ዳራ መነሻ በማድረግ፤ የኢትዮጵያ ጀግኖችንና የዓድዋ መልክዓ ምድርን በሚገልፅ መልኩ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ በመገንባቱ ረገድ፤ በተለይ በዲዛይን ማሻሻያውና በቁጥጥሩ ተግባር ላይ ኮርፖሬሽናችን (EEC) በነበረው ሙያዊ አበርክቶ፤ ጥቁር አናብስቱ አያት ቅድመ አያቶቻችን ያስመዘገቡትን የመላ ጥቁር ሕዝብ ድል፣ በዚህ ትውልድ ሌጋሲውን በልማቱ መስክ ያስቀጠለ አንጸባራቂና ህያው አሻራ በመሆኑ፤ ኮርፖሬሽናችን (EEC) ወደር የለሽ ኩራት ይሰማዋል፡፡ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በአጠቃላይ በ3.3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ4ቱም አቅጣጫዎች የተለያዩ ስያሜ የተሰጣቸው የሙዚየሙ በሮችን ጨምሮ ለመላው ጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያውያን ጀግኖች፣ የዘመን አይሽሬው ህያው ተጋድሏቸው ዘካሪ ሥራዎችን መያዙ ይታወቃል።

የዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ  እየተከበረ ይገኛል Read More Âť

Scroll to Top