Ethiopian Engineering Corporation

“የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

(መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤

የኮሪደር ልማት ሥራ ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማት ሥራ ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ብቻ በኮሪደር ልማት አማካይነት ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ መሰራቱን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶችም ተካተው መከናወናቸውን አንስተዋል ።
አክለውም በሁሉም የክልል ከተሞች አስደማሚ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በማስታወስ፤ ለአብነትም በሐረር ከተማ በዜጎች ተሳትፎ የተከናወነው ሥራ ለሁሉም ከተሞች ምሳሌ መሆን የሚችል ተግባር እንደሆነ መግለጻቸውን ጨምሮ ኢዜአ ዘግቧል።

ተቋማችን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) የመዲናችን አዲስ አበባን የኮሪደር ልማት ሥራ ጨምሮ በጂማ፣ በሐዋሳ፣ በአዳማና በቢሾፍቱ ከተሞች ባሉ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በአማካሪነት በመስራት ላይ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

Scroll to Top