Ethiopian Engineering Corporation

የዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ  እየተከበረ ይገኛል


(የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ እየተከበረ ያለው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሲሆን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

ይህን ዘመን አይሽሬና የመላው ጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፣ የድሉን ታሪካዊ ዳራ መነሻ በማድረግ፤ የኢትዮጵያ ጀግኖችንና የዓድዋ መልክዓ ምድርን በሚገልፅ መልኩ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ በመገንባቱ ረገድ፤ በተለይ በዲዛይን ማሻሻያውና በቁጥጥሩ ተግባር ላይ ኮርፖሬሽናችን (EEC) በነበረው ሙያዊ አበርክቶ፤ ጥቁር አናብስቱ አያት ቅድመ አያቶቻችን ያስመዘገቡትን የመላ ጥቁር ሕዝብ ድል፣ በዚህ ትውልድ ሌጋሲውን በልማቱ መስክ ያስቀጠለ አንጸባራቂና ህያው አሻራ በመሆኑ፤ ኮርፖሬሽናችን (EEC) ወደር የለሽ ኩራት ይሰማዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በአጠቃላይ በ3.3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ4ቱም አቅጣጫዎች የተለያዩ ስያሜ የተሰጣቸው የሙዚየሙ በሮችን ጨምሮ ለመላው ጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያውያን ጀግኖች፣ የዘመን አይሽሬው ህያው ተጋድሏቸው ዘካሪ ሥራዎችን መያዙ ይታወቃል።

Scroll to Top