Ethiopian Engineering Corporation

News

የሀዋሳ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እየተሰራ ነው

ክትትል እየተሰራ ነው ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ሀዋሳ) ፤ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) በሀዋሳ ከተማ በግንባታ ላይ ያለው የመንገድ ሥራ ግንባታ ፕሮጀክት ጥራቱን ጠብቆ በማጠናቀቅ የከተማውን የትራፊክ ፍሰት እንዲያሳልጥ  ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ላይ እንደመገኘቱ፣ ወደከተማዋ የሚመጡ ጎብኚዎችን ጨምሮ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ፣ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን ጭምር ያካተተ ነው። ይህ ፕሮጀክት 5.43 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን ለአብነትም በሎት 1 ላይ  በጠቅላላው 26 ሜትር ስፋት ያለውና በአንድ ጊዜ በሁለቱም አቅጣጫ በድምሩ ስምንት (8) ተሽከርካሪዎችን ማሳለፍ እንዲችል ሆኖ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ከሳውዝ ስፕሪንግ እስከ ሐይሌ ሪዞርት መጋጠሚያ ድረስ ያለው መንገድ የእግረኛ መንገዱን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ የአፈር ቆረጣው ሥራ ተጠናቆ፤ የመጨረሻ ንጣፍ (Base Course) ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ኮርፖሬሽናችን (EEC) በሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ላይ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ተሳትፎ እያደረገ ሲሆን ከከተማው ወደ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደውን መንገዱን ጨምሮ ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችም ላይ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ጉልህ አሻራውን ማሳረፉ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ፣ ጅማ፣ አዳማና ቢሾፍቱ ከተሞች የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ኮርፖሬሽናችን (EEC) እንደሚሳተፍ መዘገባችን ይታወቃል።

የሀዋሳ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እየተሰራ ነው Read More »

We Got Our First Private Client for the Construction Sector!!

May 21,2025 (Addis Ababa) We are delighted to announce that we have signed a contract with Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church  Client:  Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church  Consultant: Zeleke Belay Architect PLC  Scope: Construction works of the structure works of Eastern Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church 2B+G+15 multipurpose building  Amount:  803,970,655.48 ETB   Duration: 540 calendar days  Location: Addis Ababa, Ethiopia  We thank our team for their dedicated work on securing this project.  We wish good luck and success to the entire team to be involved.

We Got Our First Private Client for the Construction Sector!! Read More »

EEC የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከልን መልሶ ለማደራጀት የዲዛይንና የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራረመ

(መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤ ኮርፖሬሽኑ በትናንትናው ዕለት ማለትም መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም የውል ስምምነቱን የተፈራረመው፤ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ሲሆን የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የጂኦሳይንስ መረጃን ለማመንጨት እና የማዕድናት ናሙና መመርመሪያ በመሆን የሚያገለግለውን፤ የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከልን መልሶ ለማደራጀት የሚያስችል ተግባርን ለማከናወን ነው፡፡ የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከል፣ የጂኦሳይንስ መረጃን በማመንጨትና ማዕድናትን በመመርመር፤ ለረጅም ጊዜ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን የማዕከሉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና መልሶ ለማደራጀት፤ ከሰባት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ፤ ከኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) ጋር የፕሮጀክት ስምምነቱ ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት፣ የኮርፖሬሽናችን (EEC) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽመልስ እሸቱ (ኢንጂነር) እና የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ ተፈራመዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረትም ግንባታውን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል፡፡

EEC የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከልን መልሶ ለማደራጀት የዲዛይንና የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራረመ Read More »

“የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

(መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤ የኮሪደር ልማት ሥራ ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማት ሥራ ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ብቻ በኮሪደር ልማት አማካይነት ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ መሰራቱን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶችም ተካተው መከናወናቸውን አንስተዋል ።አክለውም በሁሉም የክልል ከተሞች አስደማሚ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በማስታወስ፤ ለአብነትም በሐረር ከተማ በዜጎች ተሳትፎ የተከናወነው ሥራ ለሁሉም ከተሞች ምሳሌ መሆን የሚችል ተግባር እንደሆነ መግለጻቸውን ጨምሮ ኢዜአ ዘግቧል። ተቋማችን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) የመዲናችን አዲስ አበባን የኮሪደር ልማት ሥራ ጨምሮ በጂማ፣ በሐዋሳ፣ በአዳማና በቢሾፍቱ ከተሞች ባሉ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በአማካሪነት በመስራት ላይ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

“የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Read More »

ለእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያ ማስፋፊያና መሪ እቅድ ንድፍ (Master Plan Design) የግብዓት ማሰባሰብ ስራ ተጀመረ

የካቲት 29, 2017 (አዲስ አበባ)፤ የኢትዮ – ጅቡቲ ባቡር መንገድ ካሉት 20 የባቡር ጣቢያዎች አንዱ የሆነው ይህ ጣቢያ ማስፋፊያውን የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) የጥናት፣ ዲዛይንና ማማከር ስራ እየሰራ ይገኛል። የግብዓት ማሰባሰቢያ አውደ ጥናት ተዘጋጅቶ ሰፊ የባለሞያዎች ውይይት ማድረግ የተቻለ ሲሆን በመድረኩም ብዙ ገንቢ ሀሳቦች ተነስተዋል። የእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያ የሚገኝበት አካባቢ ለአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ የገቢና ወጪ ንግዶችን ከማቀላጠፉ በተጨማሪ ከቢሾፍቱ ከተማ በቅርብ ርቀት እየተገነባው ያለው አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያን፣ የሞጆና የቃሊቲ ደረቅ ወደቦችን በማቀናጀት የሀገር ውስጥና የውጪ የንግድ ልውውጥን በየብስ፣ በአየርና በባህር ትራንስፖርት በማሳለጥና በማዘመን የእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያን ወደ ነጻ የንግድ ቀጠናነት (Free Trade Zone) ለማሳደግ ያለመ ፕሮጀክት ነው። ኮርፖሬሽኑ (EEC) በሀገር ውስጥና በአፍሪካ በተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ በጎ አሻራውን እያኖረ ሲሆን ይህንንም ታላቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለውን ፕሮጀክት የዲዛይን ስራውን አለም አቀፍ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርግ አስታውቋል። በቅርቡ የቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ግንባታ ፕሮጀክትን በግማሽ ቢልዮን ብር በጥራት ገንብቶ ለማስረከብ ኮርፖሬሽናችን (EEC) ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ጋር መፈራረሙን መዘገባችን ይታወሳል። 

ለእንዶዴ የጭነት ባቡር ጣቢያ ማስፋፊያና መሪ እቅድ ንድፍ (Master Plan Design) የግብዓት ማሰባሰብ ስራ ተጀመረ Read More »

የዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ  እየተከበረ ይገኛል

(የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤ 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ እየተከበረ ያለው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሲሆን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ ይህን ዘመን አይሽሬና የመላው ጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፣ የድሉን ታሪካዊ ዳራ መነሻ በማድረግ፤ የኢትዮጵያ ጀግኖችንና የዓድዋ መልክዓ ምድርን በሚገልፅ መልኩ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ በመገንባቱ ረገድ፤ በተለይ በዲዛይን ማሻሻያውና በቁጥጥሩ ተግባር ላይ ኮርፖሬሽናችን (EEC) በነበረው ሙያዊ አበርክቶ፤ ጥቁር አናብስቱ አያት ቅድመ አያቶቻችን ያስመዘገቡትን የመላ ጥቁር ሕዝብ ድል፣ በዚህ ትውልድ ሌጋሲውን በልማቱ መስክ ያስቀጠለ አንጸባራቂና ህያው አሻራ በመሆኑ፤ ኮርፖሬሽናችን (EEC) ወደር የለሽ ኩራት ይሰማዋል፡፡ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በአጠቃላይ በ3.3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ4ቱም አቅጣጫዎች የተለያዩ ስያሜ የተሰጣቸው የሙዚየሙ በሮችን ጨምሮ ለመላው ጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያውያን ጀግኖች፣ የዘመን አይሽሬው ህያው ተጋድሏቸው ዘካሪ ሥራዎችን መያዙ ይታወቃል።

የዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ  እየተከበረ ይገኛል Read More »

Scroll to Top